በፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሕብረተሰቡ ድርሻ ምን መሆን አለበት?
መንኛውም ሰው በመንግስት እውቅና በተሰጠው በህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ተሳትፎ የማድረግ መብት ሃገራችን ካፀደቀቻቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት የቃል ኪዳን ሰነዶችና በሃገራችን ህገ-መንግስት በአንቀፅ 38 ንዑስ አንቀፅ 1(ሀ) ላይ በግልፅ ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ የህብረተሰቡ በፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ የዚሁ መብት መገለጫ ነው፡፡
ለፍትህ አስተዳደሩ የሚደረገው ድጋፍ በበጎ ፈቃደኝነት ከሚደረጉ ተግባራት አንስቶ በህግ የታዘዙ ግዴታዎችን መፈፀም የሚያጠቃልል ሲሆን በህግ የተቀመጡ ግዴታዎችን ሣይፈፅሙ ሲቀሩ ግለሰቦችን በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጉ የወንጀል ድንጋጌዎች በወንጀል ህጉ ተደንግገዋል፡፡
በሃገራችን ህጎች መሰረት ህብረተሰቡ በ 3 መንገዶች በፍትህ አስተዳደሩ ተሳትፎ ወይም ድጋፍ ማድረግ ይችላል።
ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ በመስጠት
ለ) ምስክር በመሆን
ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት
ሀ) ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ መስጠት
በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ አንቀፅ 11 መሰረት ማንም ሰው ማንኛውንም ወንጀል ሲሰራ ያየ ወይም ያላየም ቢሆን የወንጀል ክስ እንዲቀርብ ወንጀሉን ለማስታወቅ መብት አለው በማለት ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ግን ወንጀል የተፈጸመ መሆኑን ማሳወቅ ግዴታ የሚሆንበት ሁኔታዎች እንዳሉ በወንጀል ህጋችን በዝርዝር ተቀምጧል እነዚህም፡-
ከአንቀጽ 241-246 እና ከአንቀፅ 252-258 የተደነገጉትን ወንጀሎች ማለትም በአገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት፣ የፓለቲካና የግዛት ሉአላዊነት ፣የመከላከያ ሃይል ወይም የውስጥና የውጭ ደህንነት ላይ ወንጀል ሲፈጽም፣ ለመፈጸም ሲሞክር ወይም ሲዘጋጅ ያያ እንደሆነ ለሚመለከተው ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት
በመከላከያ ሰራዊት እና በወታደራዊ ግዴታዎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን( ወታደራዊ ኩብላ ወይም ወታደራዊ አመፅ) የማሳወቅ ግዴታ
በሞት ወይም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀሙን ወይም የወንጀለኛውን ማንነት የማሳወቅ፣
እነዚህ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ለሚመለከተው አካል አለማሳዎቅ የወንጀል ተጠያቂነት ወይም ቅጣት አለው፡፡
በሌላ በኩል ወንጀል ያጠቃላይ ህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር እንደመሆኑ መጠን ወንጀልን መከላከልና ተፈፅሞ ሲገኝ ተጠርጣሪውን ወደ ፍትህ አደባበይ እንዲቀርብ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡
ወንጀል መፈጸሙን ጥቆማ ለፓሊስ ከማቅረብ በተጨማሪ ማንኛውም ሰው የእጅ ከፈንጅ ወንጀል እየተፈጸመ ወይም ተፈፅሞ ካየ ተጠርጣሪውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችል በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀፅ 50 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች መሟላት አለበት እነሱም፡-
ወንጀሉ እጅ ከፈንጅ የተፈፀመ መሆን አለበት
ወንጀሉ በግል አቤቱታ የሚያስቀጣ የወንጀል ዓይነት መሆን የለበትም
የተፈፀመው ወንጀል ከ3 ወር በላይ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆን አለበት
ይህ ስልጣን ለግለሰቦች የተሰጠው ፓሊስ ወንጀል የተፈፀመበት ቦታ እስከሚደርስ ድረስ ወንጀለኞች ከአካባቢው እንዳይሰወሩ ለመከላከል ሲሆን ይህም በጊዜያዊነት የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የተጠርጣሪውን ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ለፓሊስ ማስረከብ ይገባል፡፡
ለ) ምስክር በመሆን ድጋፍ ማድረግ
በወንጀልም ሆነ በፍትሃብሄር ጉዳይ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገበት ያለን ጉዳይ እልባት ለመስጠት በተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ከሚገባቸው ነገሮች ውስጥ ጉዳዮን ያስረዱልኛል የሚሉዋቸውን የምስክሮች ስም ዝርዝር እና የሰነድ ማስረጃዎችን ከክሱ ወይም ከመልሳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
ምስክርነት ማለት ግለሰቦች በፍርድ ቤት በተያዘ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ የሚያውቁትን ነገር ፍርድ ቤት በአካል በመቅረብ የአስረጅነት ቃላቸውን የሚሰጡበት አግባብ ነው፡፡
አንድ ሰው ፍርድ ቤት በመቅረብ የሚሰጠው ምስክርነት በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን፡-
መስክርነት መብት የሚሆንበት
ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት
ምስክርነት መብት የሚሆንበት አግባብ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ የጉዳዮ ባለቤቶች( ከሳሽ ወይም ተከሳሽ) ጉዳያቸውን ለማስረዳት እራሳቸው ምስክር ሆነው ሲቀርቡ ነው፡፡
በሌላ በኩል ምስክርነት ግዴታ የሚሆንበት አግባብ ሲሆን ይህም ማለት በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ምስክር ሆኖ የተጠራው ግለሰብ ፍርድ ቤት ለመገኘት ፈቃደኛ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በተያዘው ጉዳይ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት ስለሚቸገር ግለሰቡ በፓሊስ ተገዶ እንዲቀርብ በማድረግ የምስክርነት ቃሉን የሚሰጥበት አግባብ በህግ ተደንግጓል፡፡
የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመመስከር ፍቃደኛ ያልሆነ ግለሰብ በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 448 መሰረት የፍትህ እርዳታ መስጠትን እምቢ በማለት በሚል ርዕስ ሥር የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል፡፡
“ፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ነክ ሥልጣን ያለው አካል በያዘው ጉዳይ ላይ በምስክርነት ወይም በልዮ አዋቂ ምስክርነት ወይም በአስተርጓሚነት እንዲረዳ በህግ መሰረት የተጠራ ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሳይቀርብ የቀረ ወይም ለመቅረብ እምቢተኛ እንደሆነ ከሁለት ወር በማይበልጥቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡”
ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤት አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሚያውቀውን ጉዳይ እንዲመሰክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ሲደርሰው በመጥሪያው በተገለፀው ቀን እና ፍርድ ቤት በመቅረብ የምስክርነት ቃሉን በመስጥት የፍትህ አስተዳደሩን መደገፍ ይችላል፡፡
ሐ) ለፍርድ ቤቶች ተገቢው ክብር በመስጠት
በህገ-መንግስታችን የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነት መርህ ከማስከበር አንፃር ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የፍትህ ተቋም በመሆኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ክብር በመስጠት ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡ ተገቢውን ክብር ለፍርድ ቤቶች መስጠት ይገባል ሲባል ፍርድ ቤቶች በህግ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በሚወጡበት ወቅት ችሎት ማስቻያ ቦታዎች የዳኝነት ስራ መልካም አካሄድን ከሚያደናቀፍ፣ ከሚያውክ፣ ወይም የፍርድ ቤቱን ስልጣንና ክብር ዝቅ ከሚያደርጉ ተግባራት ነፃ መሆን ይገባቸዋል፡፡
አዲሱ የወንጀል ህጋችን በአንቀፅ 449 ማንም ሰው በፍ/ቤት ምርመራ ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ የሰደበ፣ ያወከ ወይም በነዚህ ላይ የዛተ እንደሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከሦስት ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡
ፍርድ ቤቱም የፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ካመነ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያዉኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ሕብረተሰባችን በወንጀል ወይም በፍትሃብሄር ፍትህ አስተዳደር ውስጥ በንቁ ሁኔታ በመሳተፍ የፍትህ አካላት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያሳኩ መርዳት ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ፍርድ ቤት ምስክር በመሆን፣ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ መረጃ ወይም ጥቆማ ለሚመለከተው አካል በመስጠት ወይም በህግ በተደነገገው አግባብ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና ለፍርድ ቤቶች ተገቢውን ክብር በመስጠት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ በፍትህ አስተዳደሪ መሳተፍ ይችላል፡፡
የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርህ እና ስርዓት
አስተዳደራዊ ውሳኔ ምንድነው?
‘አስተዳደራዊ ውሳኔ’ በአስተዳር ህግ ውስጥ ከቃል አጠቃቀም፣ ከይዘትና ከወሰን አንጻር ቁርጥ ያለ መደብ ከሌላቸው ፅንሰ ሀሳቦች መካከል ጎልቶ ይወጣል፡፡ ውስብስብነቱ ከፅንሰ ሀሳቡ ወካይ ስያሜ ይጀምራል፡፡ ‘አስተዳደራዊ ውሳኔ’ በሚል እዚህ ላይ መጠቀሱም በአገራችን የአስተዳደር ህግ ውስጥ መደበኛ መጠሪያው ቢሆን ይበጃል በሚል ብቻ ነው፡፡ ጀርመኖች እንኳን የራሳቸውን ወካይ ቃል መፍጠር ተስኗቸው አሁን ላይ በአስተዳደር ህጋቸው ዐቢይ ስፍራ ይዞ የሚገኘውን 'Administrative act' (Verwaltungsakt) በሚል የሚጠሩትን ፅንሰ ሀሳብ ለማዳበር ከፈረንሳዮች acte administrative ለመዋስ ተገደዋል፡፡
'Administrative act' (Verwaltungsakt) is a core concept of the German administrative law. It covers most of the actions of the administrative authorities through which they affect the legal interests of an individual. The origin of this concept is traced from the French concept of acte administratif from which it was borrowed by the German jurists and developed into a German concept since 1826 onwards.a
በእንግሊዝኛው ፍቺ ከወሰድነው Administrative Decision በይዘቱ Administrative Act ውስጥ የሚጠቃለል ሲሆን ዘርፈ ብዙ መልክ ካላቸው አስተዳደራዊ ተግባራት መካከል አንድ ነጠላ ተግባርን ብቻ ይወክላል፡፡ ሆኖም ለአገራችን የአስተዳደር ህግ ‘አስተዳደራዊ ተግባር’ ወይም ‘አስተዳደራዊ ድርጊት’ የሚለውን ቃል ብንጠቀም ገላጭነቱ አይጎላም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አስተዳደራዊ ድንጋጌ ማውጣት እንዲሁም ምርመራ፣ ቁጥጥርና ክትትል ሁሉም የአስተዳደር ተግባራት እንደመሆናቸው ዳኝነታዊ ባህርይ ያላቸውን ተግባራት ለይቶ ለማመልከት ውስን ይዘት ያለውን ቃል መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንጻር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ‘የአስተዳደር ውሳኔ’ ወይም ‘አስተዳደራዊ’ ውሳኔ የሚለው ቃል ዳኝነታዊ ባህርይ ያላቸውን ተግባራት ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ሆኖም በመደበኛ ትርጓሜው አደናጋሪ መልዕክት ስለሚፈጥር ይዘቱንና ፍቺውን በቅድሚያ መወሰን ያስፈልጋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1976 ዓ.ም. በወጣው የጀርመን የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ የአስተዳደር ተግባር (Administrative act) የሚከተለው ፍቺ ተሰጥቶታል፡፡
Administrative act is every order, decision or other sovereign measure taken by an authority for the regulation of a particular case in the sphere of public law and directed at immediate external legal consequences.b
ወደ አማርኛ ስንመልሰው፤
የአስተዳደር ተግባር ማለት ቅርብና ውጫዊ የህግ ውጤት የሚያስከትል በህዝብ አስተዳደር ህግ ማዕቀፍ ውስጥ አንድን ልዩ ሁኔታ ለመቆጣጠር ሲባል ስልጣን ያለው አካል የሚሰጠው ትዕዛዝ፣ ውሳኔ ወይም ሌላ ማናቸውም ሌላ ሉዓላዊ እርምጃ ነው፡፡
በትርጓሜው ውስጥ ተጨማሪ ሰፊ ማብራሪያ የሚሹ ንዑስ ሀሳቦች ታጭቀዋል፡፡ ሆኖም በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል በጀርመን የአስተዳደር ህግ የአስተዳደር ተግባር ማለት ህግ ለማስፈጸምና የአስተዳደር ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት ይህን ህዝባዊ ስልጣናቸውን (public functions) በመገልገል የሚሰጡትን ትዕዛዝ፣ ውሳኔ ወይም ማናቸውም በማድረግ፣ ባለማድረግ የሚገለጽ እርምጃ ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ይህም ማለት በውል ወይም ከውል ውጪ ኃላፊነት ህጎች ስር የሚሸፈኑ ግላዊ ድርጊቶች፣ ውሳኔዎች፣ እርምጃዎች ወዘተ…በአስተዳደር ተግባር ስር አይሸፈኑም፡፡
በትርጓሜው ላይ ‘ልዩ ሁኔታ ለመቆጣጠር’ ሲባል ተግባሩ ህጋዊ ውጤት እንደሚያስከትል ወሰኑም በአንድ ልዩ ሁኔታ ላይ ያነጣጠረ እንጂ ጠቅላላ ተፈጻሚነት እንደሌለው ያመለክታል፡፡ ስለሆነም የበታች ሠራተኛ ለበላይ ኃላፊ የሚያቀርበው የውሳኔ ሀሳብ፣ ሪፖርት ወይም የምርመራ ውጤት ራሱን ችሎ ህጋዊ ውጤት የማይከተለው በመሆኑ እንደ አስተዳደራዊ ተግባር አይቆጠርም፡፡ በአንድ ዘርፍ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ (ለምሳሌ ስጋ ሻጮች ማሟላት ያለባቸው የጥራት ደረጃ) ከላይ በተቀመጠው ትርጓሜ ውስጥ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም ተፈጻሚነቱ ሁሉንም የዘርፍ ነጋዴዎች ስለሚያቅፍ ጠቅላላነት ይታይበታል፡፡ በመጨረሻም ህጋዊ ውጤቱ በአስተዳደሩ ውስጣዊ መዋቅር ተወስኖ የሚቀር (ለምሳሌ በአንድ ነጋዴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የበላይ ኃላፊው ለበታች ሠራተኛ የሚያስተላልፈው ማሳሰቢያ) ከሆነ በአስተዳደራዊ ተግባር ውስጥ አይመደብም፡፡
የአሜሪካው የፌደራል አስተዳር ስነ ስርዓት ህግ ተፈጻሚነቱ አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (rule making) እና አስተዳደራዊ ዳኝነት (adjudication) የመስጠት ሂደቶች ላይ ነው፡፡ በህጉ ላይ በተሰጠው ፍቺ አስተዳደራዊ ዳኝነት ማለት በውጤቱ ‘ትዕዛዝ’ የሚያቋቁም የአስተዳደር ሂደት (agency process for the formulation of an order) ነው፡፡ ትዕዛዝ የሚለው ቃል በአስተዳደር ስነ ስርዓት ህጉ ላይ ፍቺ የተሰጠው ሲሆን ይዘቱ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
order means the whole or a part of a final disposition, whether affirmative, negative, injunctive, or declaratory in form, of an agency in a matter other than rule making but including licensing.c
‘ትዕዛዝ’ ከጀርመኑ ‘የአስተዳደር ተግባር’ ጋር ሲነጻጸር መሰረታዊ ልዩነት አይታይበትም፡፡ ጉዳዩን የሚቋጭ የመጨረሻ መሆኑ ህጋዊ ውጤት እንደሚከተለው ይጠቁመናል፡፡ በይዘቱ አንድ ድርጊት እንዳይፈጸም፣ እንዲፈጸም ወይም የአንድ ሁኔታ (መብት) መኖር/አለመኖር የሚያረጋግጥ መግለጫ ወይም ከአስተዳደራዊ ድንጋጌ ማውጣት ውጪ ያለ ማንኛውም የመጨረሻ እልባት የሚሰጥ ነው፡፡
በመቀጠል የአገራችን የፌደራል ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ (1993) የተጠቀመውን ቃል እና አፈታቱን እናያለን፡፡ በረቂቅ አዋጁ የትርጓሜ ክፍል አንቀጽ 2 /2/ እንደተመለከተው አስተዳደራዊ ውሳኔ ማለት፤
ማናቸውም አስተዳደራዊ ባህርይ ያለውን ተግባር ወይም ነገር ከመፈጸም ጋር የተያያዘ ውሳኔ ወይም ውሳኔ አለመስጠትን ጨምሮ ቅጣትን ለመጣል፣ ወይም መፍትሔ ለመስጠት ወይም የመከላከል ዓላማ ወይም ውጤት ያለው በአስተዳደር ተቋማት የሚሰጥ ማናቸውም ውሳኔ፣ ትዕዛዝ ወይም ብይን [ነው፡፡]
የትርጓሜውን ይዘት ይበልጥ ለመረዳት የእንግሊዝኛውን ቅጂ መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡
Administrative Decision means any decision, order or award of an agency having as its object or effect the imposition of a sanction or the grant or refusal of relief, including a decision relating to doing or refusing to do any other act or thing of an administrative nature, or failure to take a decision
በቀጣይ በ2001 ዓ.ም. በተዘጋጀው ረቂቅ የአስተዳደር ስነ ስርዓት ህግ አዋጅ አርቃቂዎቹ የተለየ አገላለጽ መጠቀም መርጠዋል፡፡ በረቂቁ አንቀጽ 2/2/ ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡፡
አስተዳደራዊ ውሳኔ ማለት ተጨባጭ ሕጋዊ ግንኙነቶችን ለመመስረት፣ ለማሻሻል፣ በምርመራ ለማረጋገጥ ወይም የተሟላ ለማድረግ ለአንድ ጉዳይ የተወሰነ መፍትሔ የመስጠት ዓላማ ያለውና በግለሰብ ወይም በተወሰኑ ሰዎች ላይ ተፈጻሚነት ያለው በተቋሙ የሚሰጥ ሕጋዊ ውሳኔ ሲሆን፣ አስተዳደራዊ ባህርይ ባለው ተግባር ወይም ጉዳይ ላይ ውሳኔ አለመስጠትንም ይጨምራል፡፡
በሁለቱም ረቂቆች ላይ የሚታየው ገላጭነት የጎደለው የቋንቋ አጠቃቀም አብዛኛው ሰው በቀላሉ አይረዳውም፡፡ ከዚህም አልፎ የህግ ባለሞያዎች፣ ዳኞች እና አስተዳዳሪዎች በጋራ የሚያግባባ አገላለጽ አልያዘም፡፡ ለምሳሌ በተለምዶ ሰርኩላር በሚል ስያሜ ጠቅላላ ተፈጻሚነት ኖሯቸው የሚተላፉ ትዕዛዞች የአስተዳደራዊ ውሳኔና የአስተዳደራዊ ድንጋጌ ከፊል ባህርያት ይጋራሉ፡፡ ሆኖም በአንደኛው ስር ለመፈረጅ ሁለቱም ትርጓሜዎች ግልጽ መለያ መስፈርት አላካተቱም፡፡ ለአስተዳደራዊ ውሳኔ ትርጓሜ ለማበጀት ጥሩ መነሻ የሚሆነው የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው፡፡ ሁለቱን የሚያመሳስላቸው ብዙ ነጥቦች አሉ፡፡ አስተዳደራዊ ሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሁለቱም ምንጫቸው ዳኝነታዊ ስልጣን ነው፡፡ በዳኝነት ፍሬ ነገሩን የማረጋገጥና በተረጋገጠው ፍሬ ነገር ላይ ህጉን ተፈጻሚ የማድረግ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ ዓላማው አከራካሪ የሆነ አንድ ተለይቶ የታወቀ ጉዳይ (particular case) መቋጨት ነው፡፡ ጉዳዩን በመቋጨት የሚነገረው ትዕዛዝ፣ ብይን ወይም ውሳኔ በባለጉዳዮች ወይም ሶስተኛ ወገኖች ላይ ህጋዊ ውጤት ያስከትላል፡፡ እነዚህ ወሳኝ ባህርያት በጀርመኑ እና የአሜሪካው የአስተዳደር ህጎች ላይ በግልጽ ተለይተዋል፡፡
በአንድ የአስተዳደር መ/ቤት የተፈጸመ ተግባር የአስተዳደር ውሳኔ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ መሰረታዊ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ጥያቄው ተቋሙ ካሉት ጠቅላላ የማስተዳደር (ህግ ማስፈጸም)፣ ከፊል የህግ አውጭነት እና ከፊል የዳኝነት ስልጣናት መካከል የትኛውን እየተገለገለ እንደሆነ የሚለይበት ነው፡፡ የጥያቄው ሌላ መልክ ሲታይ ተቋሙ የፈጸመው ተግባር በባህርዩ ዳኝነታዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ የውሳኔ ሰጭውን የስልጣን እና የተግባር ዓይነት መለየት በህጉ የአፈጻጸም ወሰን ላይ የራሱ ጉልህ እንደምታዎች አሉት፡፡ ጠቅለል ባለ አነጋገር የአስተዳደር መ/ቤቶች ዳኝነታዊ ወይም የህግ አውጭነት ስልጣናቸውን በሚገለገሉበት ጊዜ ካልሆነ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በአስተዳደር ስልጣን ውስጥ የሚወድቁት ድርጊቶች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸው አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር አስተዳደራዊ ውሳኔ ወይም ድንጋጌ ባልሆነ ጉዳይ ላይ የአጣሪ ዳኝነት ስልጣን አይኖራቸውም፡፡ የአስተዳደር መ/ቤቶች ዳኝነታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሰጡ መሰረታዊ የውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች ተፈጻሚ መሆን ይጀምራሉ፡፡
ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች የወል የዳኝነት ሥልጣን
1)የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት ላይ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል ፡
ሀ) ሕገ መንግሥቱን፣ የፌዴራል መንግሥቱን ሕጎች ወይም ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸዉ እና ያፀደቀቻቸዉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሠረት በማድረግ በሚነሱ ጉዳዮች
ለ) በፌዴራል መንግሥቱ ሕግ ተገልጸው በተወሰኑ ባለጉዳዮች፤
ሐ) በሕገ መንግሥቱ ወይም በፌዴራል መንግስት ሕግ በተገለጹ ቦታዎች፡
2) የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 9(2) እና 13(1)
መሰረት የህገ መንግስቱን ድንጋጌወች ተግባራዊ ያደርጋሉ።
4.የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን
የፌዴራልፍርድቤቶችበሚከተሉትየወንጀልጉዳዮችላይየዳኝነትሥልጣንይኖራቸዋል፡፡ 1) በአገር ላይ የሚፈፀሙወንጀሎች፣
2) በውጭ ሀገር መንግሥት ላይ የሚፈጸሙወንጀሎች፣
3)ዓለምአቀፍሕጐችንበመጣስየሚፈፀሙወንጀሎች፤
4)ከአንድ ክልል በላይ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በሚሰጡ መገናኛዎች ደህንነትና ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣
5)የበረራ ደህንነትን የሚመለከቱ ወንጀሎች፤
6) ዓለም አቀፍ የዲኘሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ ቆንስሎች፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ወይም ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተበዳይ ወይም ተከሳሽ የሆኑባቸው ወንጀሎች፣
7) የአደገኛና አደንዛዥ ዕጾች ሕገ-ወጥ ዝውውርን የሚመለከቱ ወንጀሎች፣
8) በተለያዩ ክልሎች ወይም በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክልል ሥር በሚወድቁና በተያያዙ ወንጀሎች፣
9) በተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ጎሣዎች፣ በሀይማኖት ተከታዮች ወይም በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣
10) በፌዴራል መንግሥቱ የቀረጥና የግብር ገቢዎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤
11) በፌዴራል መንግሥቱ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤
12) በታዎቁ ገንዘቦች፣የግዴታ ወይም የዋስትና ሰነዶች፣ ቴምብሮች ወይም መሳሪያዎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤
13)የዚህአዋጅአንቀጽ12ንዑስአንቀጽ(2)እናአንቀጽ15 ንዑስአንቀጽ(2)እንደተጠበቀሆኖ፤ከ5ዓመት ጽኑ እሥራት በላይ ሊያስቀጡ የሚችሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ተበዳይ ወይም ተከሳሽ የሆኑባቸው ወንጀሎች፣
14)የፌዴራልመንግሥቱባለሥልጣኖችበማናቸዉምየወንጀልጉዳዮችእናየፌደራልመንግስትሠራተኞች በሥራቸውወይምበኃላፊነታቸውምክንያትተጠያቂየሚሆኑባቸውየወንጀልጉዳዮች
15) በፌዴራል መንግሥቱ ንብረቶች ላይ በሚፈጸሙ እና የአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ (2) እና አንቀጽ
15 ንዑስ አንቀጽ (2) እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከ5 ዓመት ጽኑ እሥራት በላይ ሊያስቀጡ የሚችሉ ወንጀሎች
16) በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ በሚነሱ ማናቸዉም የወንጀል ጉዳዮች እና
17) በሌሎች ሕጐች በተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
5.የፍትሐ ብሔር የዳኝነት ሥልጣን
1)የፌዴራልፍርድቤቶችበሚከተሉትየፍትሐብሔርጉዳዮችላይየዳኝነትሥልጣንይኖራቸዋል፡ ሀ) የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱጉዳዮች፤
ለ)የውጭሀገርንፍርድወይምብይንለማስፈፀምበሚቀርብአቤቱታ፤ ሐ)ዜግነትንበሚመለከቱጉዳዮችላይበሚነሱክርክሮች፣
መ) ከመክሰር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች
ሠ) ዓለም አቀፍ የዲኘሎማቲክ ሕጐችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሆኑባቸው ወይም/እና ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተከራካሪ በሆነበት ጉዳዮች፣
ረ) የፌዴራል መንግሥት አካል ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
ሰ) የፌዴራል መንግሥቱን ንብረቶች የተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፤
ሸ) መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች፣ በክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ፣ በክልል እና በድሬዳዋ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ጉዳዮች፣
ቀ) የፌዴራል መንግሥቱ ባለሥልጣኖችና ሠራተኞች በስራቸዉ ወይም በሃላፊነታቸዉ ምክንያት ኃላፊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣
በ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ (2) እና አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (2) ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የውጭ አገር ዜጋ ከሳሽ ወይም ተከሳሽ የሆነበት ጉዳይ፤
ተ) በፌዴራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች፣
ቸ) የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች ፤
አ) በፈጠራ፣ በድርሰትና ሥነ ጥበብ፣ ቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤትነት በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች፣
ነ) የኢንሹራንስ ውልን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች፣
ኘ)ተገዶየመያዝሕጋዊነትንለማጣራትየሚቀርብ አቤቱታ
ደ)በአዲስአበባእናድሬዳዋከተሞችየሚነሱየፍታብሄርጉዳዮችእና ጀ) በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱጉዳዮች፡፡
2) የክልል ጉዳይ በክልሉ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ ወይም ከተወሰነ በኋላ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 «ሸ» እና «ነ» ላይ የተጠቀሰ ተከራካሪ በማንኛውም ሁኔታ ወደ ክርክሩ ቢገባ እንኳ ጉዳዮ በክልሉ ፍርድ ቤት መታየቱ ይቀጥላል፡፡
6.የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለሚሠሩባቸው መሠረታዊ ሕጎች
1. የፌዴራልፍርድቤቶችየሥልጣንክልላቸውንመሠረትአድርገውየሚቀርቡጉዳዮችንወይምክርክሮችን ቀጥሎ የተጠቀሰውን መሠረት አድርገውይዳኛሉ
ሀ)ህገመንግሥቱን፣የፌዴራልመንግሥቱንሕጐችናኢትዮጵያአባልየሆነችባቸዉንዓለምአቀፍ ስምምነቶች
ለ)ጉዳዩየክልል፣የአዲስአበባወይምድሬዳዋከተሞችንሕግየሚመለከት ሆኖሲገኝየክልሉንወይምየከተማውንሕግ፡፡
7.የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለሚሠሩባቸው የሥነ ሥርዓት ሕጎች
በሥራ ላይ ያሉ የወንጀል እና የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑ ድረስ እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች በዚህ አዋጅ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
ምእራፍ ሦስት
ስለ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን8.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን፣
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚከተሉት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፤
1) በሕግ በሚወሰነው መሠረት አንድ ጉዳይ ከአንድ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ወደ ሌላ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ወይም በውክልና ለክልል ፍርድ ቤቶች የተሰጡ የፌዴራል
ጉዳዮችን በሚመለከት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲዛወር በሚቀርብ ጥያቄ እና
2) በሌሎች ህጎች በተጠቀሱ ጉዳዮች።
9.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ የዳኝነት ሥልጣን
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚከተሉትን ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ሥልጣን ይኖረዋል፤
1) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣኑ ውሣኔ የሰጠባቸው፣
2) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሰሚነት ሥልጣኑ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው ፣
3) የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ጉዳዩችን በተወካይነቱ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ አይቶ ውሳኔ የሰጠባቸው፣
4) የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በይግባኝ ሰሚነት ሥልጣኑ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው፣
5) በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱ ጉዳዮችን፡፡
10.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥልጣን
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ያለባቸውን የሚከተሉትን ጉዳዮች በሰበር የማየት ሥልጣን ይኖረዋል።
ሀ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ፤
ለ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የመጨረሻ ውሣኔ የሰጠባቸው፤
ሐ) የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (4)(ሀ) እና (ሸ) ን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው፣
መ) የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (4)(ለ) በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው እና ጉዳዮቹ ሰፋ ያለ ህብረተሰብ ክፍል መብቶችን ሊመለከቱ የሚችል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ሲሆኑ
ሠ) የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወይም የየክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በህገ መንግስቱ በተሰጣቸዉ የዉክልና ስልጣን የፌደራል ጉዳይን አይተዉ የመጨረሻ ዉሳኔ የሰጡበት፤
ረ) የአዲስ አበባ ወይም የድሬዳዋ ከተማ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ፤
ሰ) በሕግ የመዳኘት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በሌሎች አካላት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ፤
ሸ)አግባብነትያላቸውየህግድንጋጌዎችእንደተጠበቁሆነዉ፤በፌዴራልፍርድቤትሊታይይችልበነበረ ጉዳይላይበአማራጭየክርክርመፍቻዘዴዎችመሠረትየተሰጠየመጨረሻውሳኔ፤
ቀ) በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
2) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1(መ) እና የዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (4)(ሀ) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጋር ተያይዞ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ፣ በማህበራዊ ፍርድ ቤት በተጀመሩ አነስተኛ ጉዳዮች ላይ የሚሰጥ የመጨረሻ ውሳኔ ወይም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚጠቀሱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ በሚሰጥ የመጨረሻ ዉሳኔ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አይቀርብም፡፡
3) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠውየሕግትርጉምውሳኔውከተሰጠበትቀንጀምሮበየትኛዉምደረጃበሚገኝየፌደራልም ሆነየክልልፍርድቤትአስገዳጅነትይኖረዋል፡፡
4) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ችሎቶች አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የተሰጠባቸውን ውሳኔዎች በኤሌክትሮኒክስ ወይም በህትመት ሚዲያዎች በተቻለ ፍጥነት ያሰራጫል።
ምእራፍ አራት
ስለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት
ሥልጣን
11.የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐ ብሔር የዳኝነት ሥልጣን
1) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግምታቸዉ ከአስር ሚሊዮን (10,000,000 birr) በላይ በሆኑ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፤
ሀ) የዚህአዋጅበአንቀጽ14እንደተጠበቀሆኖ፣በዚህአዋጅአንቀጽ3እና5 መሰረትበሚነሱማናቸዉም የፍታብሄርጉዳዮች።
ለ) በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በሚነሱ ማናቸዉም የፍታብሄር ጉዳዮች፡፡
2) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1)(ሀ) ቢኖርም፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚከተሉት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፤
(ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ (1)(ሀ) እስከ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሠ) ላይ በተጠቀሱት የፍትሐብሔርጉዳዮች፤
(ለ) በሕግ በሚወሰነው መሠረት አንድን ጉዳይ ከአንድ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎት ወደ ሌላ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎት ወይም ወደ ራሱ እንዲዛወር የሚቀርብን ጥያቄ፤
(ሐ) በሌሎችህጐችየተጠቀሱጉዳዮች፡፡
3) በዚህ አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተመለከተዉ ቢኖርም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤትበፍርድታይተዉሊዎሰኑየሚችሉበህገመንግስቱምዕራፍሶስትስርየተመለከቱመሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን ለማስከበር ለጉዳዩ ተገቢ የሆነ ፍርድ፣ትዕዛዝ ወይም ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን አለዉ።
4) ማንኛዉም በጉዳዩ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ ሰዉ ወይም ጉዳዩን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ ሰዉ መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን ለማስከበር ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ መብት አለዉ።
5) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 እና 4 የተጠቀሰዉ ጉዳይ የሚስተናገደዉ የፍታብሄር ስነ-ስርዓት ህግ ስለ አጭር ሁኔታ በሚወሰኑ ክርክሮች ላይ ስለሚፈጸሙ ስነ-ስርዓት በሚል በተደነገገዉ መሰረት ይሆናል።
12.ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚከተሉት የወንጀል ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፣
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 4 ላይ የተመለከቱና አግባብነት ባላቸው ሕጐች መሠረት ለከፍተኛፍርድቤትበተሰጡበፌዴራልየወንጀልጉዳዮች፤
2) በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተሞች ውስጥ በሚነሱና አግባብነት ባላቸው ሕጐች መሠረት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚቀርቡ በሌሎች የወንጀል ጉዳዮች እና
3) በሌሎችሕጐችለፌዴራልፍርድቤትበተሰጡየወንጀልጉዳዮች፡፡
13.የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ዳኝነት ሥልጣን
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚከተሉትን የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ሥልጣን ይኖረዋል፡
1) የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ እና
2) በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱ ጉዳዮችን፡፡
14.የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ዳኝነት ሥልጣን
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 11 ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐ ብሔር የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 5 መሠረት በሚቀርቡ የፌዴራል የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች፤
2) በሕግ ለሌሎች አካላት የተሰጠው የዳኝነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሚነሱ ሌሎች የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች፣ እና
3) በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱ የፍታብሄር ጉዳዮች፡፡
15.የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወንጀል የመጀመሪያ የዳኝነት ሥልጣን
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚከተሉት የወንጀል ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል።
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 4 ላይ የተመለከቱና አግባብነት ባላቸው ሕጐች መሠረት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የማይቀርቡ በፌዴራል የወንጀል ጉዳዮች
2) በሕግ ለሌሎች አካላት የተሰጠው የዳኝነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአዲስ አበባ ወይም ድሬዳዋ ከተሞች ውስጥ በሚነሱ እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማይታዩ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች እና
3)በሌሎች ሕጐች የተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
16.የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የይግባኝ ስልጣን
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አግባብነት ባላቸዉ ህጎች በግልጽ በተሰጡት ጉዳዮች ላይ በይግባኝ የማየት ስልጣን ይኖረዋል።
ምእራፍ አምስት
ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ኘሬዚዳንቶች፣ ም/ኘሬዝዳንቶች፣የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች እና
ሰብሳቢ ዳኞች
17.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት በሕግ መሠረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ለማስተዳደር ኃላፊ ይሆናል/ትሆናለች፡፡
1) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትኘሬዚዳንትስልጣንእናተግባራትይኖሩታል/ይኖሯታል፡
ሀ) ለፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞችን፣ የምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞችን እና ሰብሳቢ ዳኞችን መደልደል፣ ሥራ መስጠት፣
ለ) ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን መቅጠር፣
ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ(2)(ሠ) ላይ የተጠቀሰውን ጨምሮ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ/ታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረብ፣ ሲፀድቅም ሥራ ላይ ማዋል፣
መ)በዚህአዋጅላይበተጠቀሰውመሠረትበፌዴራልጠቅላይፍርድቤትመውጣትያለባቸውደንቦች እናመመሪያዎችእንዲዘጋጁናእንዲወጡበማድረግተግባራዊመሆናቸውንማረጋገጥ፤
ሠ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ሥልጣን በውክልና ለሚሰሩ የክልል ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ ጥያቄ ላይ ውሳኔ መስጠት፤
ረ) የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ጉዳዮችን አስመልክቶ በውክልና ስላከናወኑት ተግባር በስታስቲክስ የተደገፈ ሪፖርት ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ማድረግ፣
ሰ) የዳኞችና የሌሎች ሠራተኞች ትምህርትና ሥልጠና የሚካሄድበትን ሁኔታ እንደአስፈላጊነቱ ማመቻቸት፣ ሸ) በክልል ስለሚታዩ የፌዴራል ጉዳዮች የመዝገብ አያያዝና ጠቅላላ አሠራር ከክልል ፍርድ ቤቶች ጋር
መመካከር የሚሻሻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
ቀ)ስለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የበጀት አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፓርትማቅረብ፣
በ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ተቋም ፣ የተከላካይ ጠበቆችን ቢሮ እና በሕግ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ተግባራትን ለማስፈፀም የሚያስችሉ የሥራ ክፍሎች እንዲደራጅ ማድረግ፤
ተ) የፌዴራል ፍ/ቤቶች ዳኞች ስልጠና መመሪያ ማዉጣት።
ቸ) ለኢትዮጵያ የዳኝነት ሥርዓት እድገት፤ ቀልጣፋ አሰራር እና ውጤታማነት የሚያግዙ ጥናቶች እንዲደረጉ ማድረግ፤ ተግባራዊነታቸው መከታተል፤
ነ) እንደአስፈላጊነቱ የፌዴራል ሸሪአ ፍርድ ቤቶች በተቋቋሙበት አዋጅ መሠረት የዳኝነት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ድጋፍ መስጠት
ኘ) በሕግ እና በዚህ አዋጅ የተሰጡ ሌሎች ተግባሮች ማከናዎን፡፡
18.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት የሚከተሉት ስልጣን እና ተግባር ይኖሩታል/ሯታል።
1) በኘሬዝዳንት የሚመራለትን/ላትን ሥራ ማከናዎን፣
2) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት በማይኖርበት/ትኖርበት ጊዜ ኘሬዚዳንቱን/ቷን ተክቶ መስራት፤
19.ስለፌዴራልከፍተኛእናየመጀመሪያደረጃ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትናምክትል
ኘሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር
1) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የመምራት እና ክትትል የማድረግ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የየፍርድ ቤቱኘሬዚዳንቶች፣
ሀ) ፍርድ ቤቱን ይወክላሉ
ለ) የፍርድ ቤቱን ዳኞች ይደለድላሉ፣ ሥራ ይሰጣሉ፣ ያስተዳድራሉ፣ ለ) የፍርድ ቤቱን ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ያስተዳድራሉ፣
ሐ) የየፍርድ ቤቱን ፋይናንስ ያስተዳድራሉ
መ) በሕግ እና በዚህ አዋጅ የተሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡
2) የፍርድ ቤቱን ዕቅድና በጀት አዘጋጅተው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ያቀርባሉ ፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይያውላሉ፣
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የታቀዱ ስራዎች ቀልጣፋ እና ዉጤታማ በሆነ መንገድ እንዲከናዎኑጠቅላይፍርድቤትበሚዘረጋዉየተጠያቂነትስርዓትየሚመዘንይሆናል።
4) ስለ ፍርድ ቤቱ ሥራ እንቅስቃሴ በየጊዜው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ሪፖርት ያቀርባሉ፣
5) የፌዴራል የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የየራሳቸው ምክትል ኘሬዚዳንቶች ይኖሯቸዋል፡፡
6) የየፍርድ ቤቱ ምክትል ኘሬዚዳንቶች የፍርድ ቤቱ ኘሬዚዳንት በማይኖሩበት ጊዜ በመተካት ይሰራሉ፤ እንዲሁም በኘሬዚዳንቱ የሚሰጡ ሌሎች ሥራዎች ያከናውናሉ።
7) የፌዴራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ኘሬዝዳንቶች እና ምክትል ኘሬዝዳንቶች በፍርድ ቤቶቻቸው በሚገኙ ማናቸዉም ችሎቶች ሰብሳቢ ዳኛ ሆነው ሊያስችሉ ይችላሉ።
20.ስለ ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ሥልጣንና ተግባር
1) የፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤቶች በሚያስችሉበት ምድብ ችሎቶች የየራሳቸዉ ተጠሪ ዳኛ ይኖራቸዋል፡፡
2) የየምድብ ችሎቶቹ ተጠሪ ዳኞች ከዳኝነት ሥራ በተጨማሪ ከየፍርድ ቤቶች ኘሬዝዳንቶች በሚሰጧቸዉየስራመመሪያመሰረትየሚከተሉትንተግባራትያከናዉናሉ።
ሀ) የምድብ ችሎቶቹን ሥራ ማስተባበር፤
ለ) ለሚቀርቡ አስተደደራዊ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት፣ ሠራተኞችን ማስተዳደር፤
ሐ)በምድብችሎቶቹስለተከናወኑሥራዎችለየፍርድቤታቸውኘሬዝዳንትሪፓርትማቅረብ፣ መ)የየፍርድቤቱኘሬዝዳንትየሚሰጧቸዉንሌሎችተግባራትማከናዎን፡፡
3) የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት በሚሰጣቸዉ ዉክልና መሰረት የምድብ ችሎቱን ፋይናንስ ማስተዳደር።
21.ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤት የችሎት ሰብሳቢ ዳኛ
ሶስትና ከሶስት በላይ የሆኑ ዳኞች በሚያስችሉበት የፌዴራል ፍርድ ቤት ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ይኖረዋል፡፡
22.የፌዴራል ፍርድ ቤት ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ተግባር
1) የፌዴራል ፍርድ ቤት ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናዉናል/ታከናዉናለች ሀ) የችሎቱ ሥራ በህግ መሠረት መመራቱን በማረጋገጥ ችሎቱን ማስተዳደር
ለ)በችሎቱየሚወሰኑመዝገቦችበሁሉምየችሎቱዳኞችግንዛቤየተወሰደባቸውመሆኑንማረጋገጥ፣ ሐ)ለችሎቱየተመደቡድጋፍሰጭሰራተኞችንማስተዳደር
መ) ሁሉም የችሎቱ ዳኞች በችሎቱ የሚሰጡ ውሳኔዎችን በማዘጋጀት ተመጣጣኝ ተሳትፎ ማድረጋቸውንመከታተል፡፡
2) ሰብሳቢ ዳኛው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱትን ተግባራት የችሎቱን ዳኞች የዳኝነት ነፃነት በማይጋፋ ሁኔታ ይፈጽማል/ትፈጽማለች፡፡
ምእራፍ ስድስት
ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች አደረጃጀትና የዳኝነት ሥራ አካሄድ
23.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ሌሎች ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ኘሬዚዳንት፣ አንድ ምክትል ኘሬዝዳንት እንዲሁም የዳኝነት ስራዉን ለማከናዎን አስፈላጊ የሆኑ ዳኞች ይኖሩታል፡፡
2) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚያስተዳድራቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳይሬክተሮች፣ ሬጅስትራሮች፣ የዳኛ ረዳቶች ፣ የህግ ባለሙያዎች እና ሌሎች ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡
24.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎቶች
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የፍታብሄር እና የወንጀል የመጀመሪያ ደረጃ፣ ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎቶች ይኖሩታል፡፡
2) በእያንዳንዱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከ3 (ሶስት) ባላነሱ ዳኞች የሚያስችሉ ሲሆን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎቶች ደግሞ ከ 5 (አምስት) ባላነሱ ዳኞች ያስችላሉ፡፡
3)የፌዴራልጠቅላይፍርድቤትኘሬዝዳንትእናምክትልኘሬዝዳንትበጠቅላይፍርድቤትበሚገኙ ማንኛዉምችሎትሰብሳቢዳኛሆነውሊያስችሉይችላሉ፡፡
25.ከሰባት ያላነሱ ዳኞች ስለሚሰየሙበት የሰበር ችሎት
1) አምስት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት በባለጉዳዮቹ አመልካችነት ወይም በችሎቱ በራሱ አነሳሽነትቀድሞየተሰጠዉንአስገዳጅየህግትርጉምበተለያዩምክንያቶችማሻሻልአስፈላጊሆኖ ካገኘዉ ከሰባት ባላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ በቂ እና አሳማኝ ምክንያቶችንተንትኖበመግለጽለፌደራልጠቅላይፍርድቤትፕሬዝዳንትማቅረብይችላል።
2) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 በተገለጸዉ መሰረት ጥያቄ ሲቀርብለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የሚሰየሙበት የሰበር ችሎት ጉዳዩን እንዲታይ ያደርጋል።
3) በዚህ አንቀጽ የተገለጸዉ የሰበር ችሎት የሚሰጠዉ የህግ ትርጉም ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማንኛዉም ደረጃ ለሚገኝ ፍርድ ቤት አስገዳጅ ይሆናል።
4) በዚህ አንቀጽ መሰረት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ቀድሞ የሰጠዉን የህግ ትርጉም ከሰባት ባላነሱ ዳኞች በተመሳሳይ ጭብጥ በሌላ ጊዜ ሊሻሻል ይችላል።
26.የሰበር አቤቱታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት
1) ለሰበር ችሎት የሚቀርብ የሰበር ማመልከቻ በውሳኔው ላይ የተፈፀመውን መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ (4) ላይ ከተሰጠው ትርጉም አንፃር ተገናዝቦና የሚጠየቀውን ዳኝነት በሚገልፅ መልኩ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን በተመለከተ በሚያወጣውመመሪያመሠረትበአጭሩተፅፎመቅረብአለበት፡፡
2) የሚመለከተው አቤት ባይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) በተጠቀሰው መሠረት ከሚያቀርበው ማመልከቻው በተጨማሪ የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ እና የበታች ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅጂዎችን ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ በስር ፍርድ ቤት ያለዉ ሙሉ መዝገብ ቅጅ እንዲቀርብለት ያደረጋል።
3) የሰበር ጥያቄ ማመልከቻ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቅረብ የሚገባው የሰበር ጥያቄ በሚቀርብበት ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሣኔ ከተሰጠ ጀምሮ ባሉት 90 (በዘጠና) ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
27.የሰበር አቤቱታን በሰበር ሰሚ ችሎት ስለማየት
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ክርክር አመራር ሥነሥርዓትን በተመለከተ የሚያወጣው ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 1ዐ መሠረት አቤቱታ በሰበር የሚሰማው አስቀድሞ ሶስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት ውሳኔው በዚህአዋጅአንቀጽ2 ንዑስአንቀጽ(4)እናአንቀጽ10ላይበተመለከቱትመሠረትለሰበርችሎት መታየት አለበት ብሎ ሲወሰንነው፡፡
2) የሰበር ችሎቱ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) መሰረት የተመራለትን ጉዳይ መርምሮ አቤቱታ በቀረበበት ጉዳይ ላይ የተፈፀመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለመኖሩን ከተረዳአቤቱታውን ውድቅ በማድረግ ትዕዛዝይሰጣል፡፡
3) የሰበር ችሎቱ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) መሰረት የተመራለትን ጉዳይ መርምሮ አቤቱታ በቀረበበት ጉዳይ ላይ ያስቀርባል ብሎ ከተረዳ ጭብጥ በመያዝ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት በአመልካች ከቀረበው የሰበር ማመልከቻ እና መጥሪያ ጋር ይልካል፡፡
4) ተከራካሪዎች መልስ እና የመልስ መልስ ክርክራቸውን በፅሁፍ አቅርበው ከተቀባበሉ በኋላ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ተከራካሪዎችን መስማት ካላስፈለገው በስተቀር በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
28.የፌዴራልከፍተኛፍርድቤትእናየፌዴራልየመጀመሪያደረጃፍርድቤቶችዳኞች፣
ችሎቶችና ሌሎች ሠራተኞች
1) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሥራቸው አስፈላጊ የሆኑ ዳኞችና ችሎቶች ይኖሯቸዋል፡፡
2) የፌዴራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በዚህ አዋጅ አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ (1) (ለ) እና አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የየፍርድ ቤቱ ኘሬዝዳንቶች የሚያስተዳድሯቸው ሬጅስትራሮች ፣ የዳኞች ረዳቶች ፣ የህግ ባለሙያዎች እና ሌሎች ሠራተኞች ይኖሯቸዋል፡፡
3) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎቶች በአንድ ዳኛ ያስችላሉ፡፡
4) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 እንደተጠበቀ ሆኖ
ሀ) ከ15 አመት በላይ የሚያስቀጡ የወንጀል ጉዳዮች በሶስት ዳኞች ይታያሉ
ለ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው መመሪያ የተወሰኑ ጉዳዮች በፌዴራል ከፍተኛ እና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሶስት ዳኞች እንዲታይ ሊደረግ ይችላል፡፡
29.ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች የማስቻያ ሥፍራ
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስቻያ ሥፍራ አዲስ አበባ ይሆናል፡፡
2) የፌዴራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የማስቻያ ስፍራ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በድሬዳዋከተማእናበፌዴራልከፍተኛፍርድቤትማደራጃአዋጅቁጥር322/95በተመለከቱት ክልሎች መሠረት እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78 ንዑስ አንቀጽ (2) ወደፊት ሊወሰኑ በሚችሉ ቦታዎችይሆናል፡፡
3) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 በተመለከቱት ቦታዎች የፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን ያደራጃል።
30.የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ቋንቋ
1) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ቋንቋ አማርኛ ይሆናል፡፡
2) የአማርኛ ቋንቋ ለማይችል ሰው ፍርድ ቤቱ ብቃት ያለው አስተርጓሚ ይመድብለታል፡
3) የምልክት ቋንቋ ለሚጠቀም አካል ጉዳተኛ በተመሣሣይ የምልክት ቋንቋ ችሎታ ያለዉ ባለሙያ ይመደብለታል፡፡
4) በየደረጃዉ ያሉ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የአስተርጓሚ ቢሮ ያደራጃሉ።
31.በግልጽ ችሎት ስለማስቻል
1) ፍርድ ቤቶች ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ያስችላሉ፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ቢኖርም ሀ) የተከራካሪዎቹን የግል ህይዎት፣
ለ) የሀገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ፣
ሐ) የሕዝብ ሞራል ሁኔታ ወይም ግብረገብነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍርድ ቤቶች በዝግ ችሎት ያስችላሉ፡፡
32.የዳኞች ከችሎት መነሳት
1) የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ከዚህ ቀጥሎ ከተመለከቱት ምክንያቶች በአንዱ ከችሎት ይነሳል/ትነሳለች።
ሀ)ከተከራካሪዎቹከአንደኛዉ/ዋ ወገንወይምከጠበቃዉ/ዋ ጋርየሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው/ያላትእንደሆነ፣
ለ) ከተከራካሪዎቹ የአንደኛዉ/ዋ ወገን ሞግዚት፣ ነገረ ፈጅ ወይም ጠበቃ በሆኑበት ጉዳይ ላይ የተነሳ ክርክር እንደሆነ፣
ሐ) ክርክር የተነሣበትን ጉዳይ አስቀድሞ በዳኝነት፣ በግልግል ዳኝነት፣ በዕርቅ ያየዉ/ያየችዉ ሆኖ ከተገኘ። ሆኖም አግባብ ባለዉ የስነ ስርዓት ህግ መሰረት የይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በይግባኝ የቀረበለትን ጉዳይ ቀድሞ ወደወሰነዉ ፍርድ ቤት በመመለስ ሂደት ጉዳዩ የተመራለት ዳኛ ላይ ይህ ተፈጻሚ አይሆንም።
መ) ከተከራካሪዎቹ ወገኖች ከአንደኛዉ/ዋ ወይም ከጠበቃዉ/ዋ ጋር በፍርድ ቤት የተያዘ ክርክር ወይም ሙግት ያለዉ/ያላት እንደሆነ፤
ሠ) ከዚህ በላይ ከንዑስ አንቀጽ (1) (ሀ) እስከ (1)(መ) ከተመለከቱት ምክንያቶች ውጭ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጥም/አትሰጥም የሚያሰኝ ሌላ በቂ ምክንያት ሲኖር፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ዳኛው/ዋ በችሎት ላይ ሊቀመጥ/ልትቀመጥ የማይገባዉ/ት መሆኑን ሲያዉቅ/ስታዉቅ ከችሎት ተነስቶ/ታ ሌላ ዳኛ መተካት አለበት/ባት፡
33.ዳኛ ከችሎት እንዲነሳ/እንድትነሳ ስለማመልከት
1) ከተከራካሪዎች አንደኛው/ዋ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 31 በተዘረዘሩት ምክንያቶች ዳኛ ከችሎት መነሳት ያለበት/ባት እንደሆነ ይህንኑ በሚመለከት ለፍርድ ቤቱ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል/ትችላለች፡
2) ማመልከቻው የሚቀርበው ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ወይም ማመልከቻ ለማቅረብ ምክንያት መኖሩን አመልካቹ/ቿ እንዳወቀ/ች ወዲያውኑ መሆን አለበት፡፡
3) ዳኛው/ዋ ብቻቸውን/ዋን የሚያስችል/የምታስችል ከሆነ እና ከችሎት ስለመነሳት የሚቀርበውን ማመልከቻ ተመልክቶ/ታ ጥያቄውን የተቀበለ/ች እንደሆነ ከችሎት ይነሳል/ትነሳለች፡፡ጥያቄውን ያልተቀበለ/ች እንደሆነ ግን በዚያው ፍርድ ቤት በሚገኝ ሌላ ችሎት፤ ሌላ ችሎት ከሌለ የዚህኑ ፍርድቤትውሣኔይግባኝበሚያየውፍርድቤትእንዲወሰንይተላለፋል፡፡
4) ከችሎት እንዲነሳ/እንድትነሳ ማመልከቻ የቀረበለት/ላት ዳኛ ከሌሎች ዳኞች ጋር የሚያስችል/የምታስችል ከሆነ ማመልከቻው በዚያው ችሎት ባሉ ሌሎች ዳኞች ይወሰናል።
5) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት የሚቀርብ ጥያቄ ለአዲሱ ችሎት በደረሰ በ15(አሥራ አምስት) ቀን ውስጥ መወሰን ያለበት ሲሆን የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻና ይግባኝ የማይባልበት ይሆናል፡፡
6) የሚሰጠውን ውሣኔ ዳኛው ወዲያውኑ መፈጸም አለባቸው፡፡
34.ማመልከቻው ስለሚያስከትለው ኪሣራ እና ቅጣት
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 32 መሠረት የሚቀርበውን ማመልከቻ ፍርድ ቤቱ ተገቢ አይደለም በማለት ሳይቀበለው ከቀረ የጉዳዩ ውጤት ከግምት ሳይገባ ኪሣራውን የሚከፍለዉ/ምትከፍለው ማመልከቻውን ያቀረበዉ/ችው ሰው ይሆናል/ትሆናለች፡፡
2) ከተከራካሪዎቹ አንደኛዉ/ዋ ወገን ዳኛው/ዋ ከችሎት እንዲነሳ/እድትነሳ ያቀረበዉ/ችው ማመልከቻ በቂ ምክንያት የሌለዉ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻዉ/ዋን ውድቅ በማድረግ በአመልካቹ/ቿ ላይ ከአንድ ሽህ ብር ያላነሰ ከአምስት ሽህ ብር ያልበለጠ መቀጫ ሊጥል ይችላል፡፡ሆኖም አቤቱታ አቅራቢዉ ሆን ብሎ የዳኛዉን ስም ለማጥፋት ወይም ክብር ለመጉዳት ወይምጉዳዮችንለማጓተትዳኛውከችሎትእንዲነሳ/እንድትነሳአቤቱታያቀረበ/ችእንደሆነፍርድ ቤቱከ5,000 ብርያላነሰ-10,000ብርያልበለጠመቀጫሊጥልይችላል።
ምእራፍ ሰባት
ስለፌደራል ፍርድ ቤቶች በጀትና የሰው ሀብት አስተዳደር
35.የፌደራል ፍ/ቤቶች የበጀት አስተዳደር ነፃነት
1) የፌዴራል ፍ/ቤቶች ከመንግሥት በጀት ላይ ጥቅል የሆነ የፍርድ ቤት ፈንድ ይመደብላቸዋል፡፡
2) የሚመደበው ጥቅል የሆነ ፈንድ፤ለፌዴራል ፍ/ቤቶች በሕገ-መንግስትና በሌሎች ሕጎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችል መሆንአለበት፡፡ ጥቅል በጀቱም የሚከተሉትንይጨምራል፤
ሀ. ለዳኞችና ከዳኞች ዉጭ ላሉ ሰራተኞች በቂ ደመዎዝና ጥቅማ ጥቅም ለመክፈል የሚያስችል፤ ለ.አስፈላጊየሆኑትንየሥራማከናወኛመሳሪያዎችንናአገልግሎቶችንለመግዛትየሚያስችል፤እና ሐ.የካፒታልዕቃዎችንእናመሰረተልማቶችንለማሟላትየሚያስችል፤
3) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 እንደተጠበቀ ሆኖ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎትየሚከፈልየዳኝነትክፍያ፣ከቅጣትየሚገኝገቢ፣ከለጋሾችየሚገኙየገንዘብእናሌሎች ለፍርድቤትየሚከፈሉክፍያዎችበፍርድቤቶችየተጠቃለለፈንድዉስጥገቢይደረጋሉ።
4) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አማካይነት ለፌዴራል ፍ/ቤቶች የጸደቀ በጀት በበጀት አርዕስት እና ተመሳሳይ መለኪያዎች ሳይወሰን የውስጥ የበጀት ሽግሽግ መብታቸው ተጠበቆ በዕቅድ ላይ በመመሥረት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች በነፃነት ከሥራ ላይ ያውሉታል።
5) ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚመደበዉ በጀት የፌደራል መንግስቱ አመታዊ በጀት ዉስጥ ከአንድ መቶኛ ያላነሰ መሆን አለበት።
36.ስለ ፌደራል ፍርድ ቤቶች በጀት
1) በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 79 (6) በተደነገገው መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የፌዴራል ፍ/ቤቶችን በጀት አዘጋጅቶ/ታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል/ታቀርባለች፡፡
2) የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ከሌሎች የፍርድ ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ የበጀት ጥያቄውን/ዋን ያስረዳል/ታስረዳለች፡፡
3) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የጸደቀላቸውን በጀት አጠቃቀም አስመልክቶለሕዝብተወካዮችምክርቤትሪፖርትያቀርባል/ታቀርባለች፡፡
4) የፌዴራል ፍ/ቤቶች የበጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥቱ የበጀት ዓመት ይሆናል፡፡
37.የፌደራል ፍርድ ቤቶች የስራ ጌዜ
1) የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና ዳኞች የስራ ሰዓት ከሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች የስራ ሰዓት ጋር ተመሳሳይ ይሆናል።
2) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተመለከተዉ ቢኖርም የፌደራል ፍርድ ቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ 1
እስከ መስከረም 30 ድረስ ዝግ ይሆናሉ።
3) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተመለከተዉ ቢኖርም በትርፍ ጊዜ በሚሰሩ ዳኞች ፍርድ ቤቶቹ ከስራ ጊዜ ዉጭ አስቸኳይ ጉዳዮችን አንዲያስተናግዱ ሊደረግ ይችላል። ። ዝርዝሩጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያይወሰናል።
38.የሰው ሀብት
1) የፌዴራል ፍ/ቤቶች የእራሳቸውን ከዳኞች ዉጭ ያሉ ሠራተኞችን የመመልመል፣ የመቅጠርና የማስተዳደር ነፃነት አላቸው፡፡
2)ከዳኞች ዉጭ ያሉ ሰራተኞች ምልመላ፣ ቅጥር፣ ምደባ፣ ዕድገት፣ ዝውውር፣ሥልጠና፣ የደመወዝ ጭማሪ፣የጥቅማጥቅምክፍያ፣የሰራተኞችየዲሲፕሊንጉዳይእናተያያዥጉዳዮችየሚወሰነው በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተዘጋጅቶ በዳኝነት አስተዳደር ጉባኤው በሚጸድቅ ደንብ አማካይነት ይሆናል፡፡
3) በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚወጣዉ ደንብ የሚከተሉትን ይጨምራል፤
ሀ. ምልመላ፣ ቅጥር፣ ምደባ፣ ዕድገት፣ ዝውውር፣ሥልጠና፣ የደመወዝ ጭማሪ፣ የጥቅማ ጥቅም ክፍያ እና የሰራተኞች የዲሲፕሊን ጉዳይ ከማንኛዉም ወገንተኝነት በጸዳ ሁኔታ መከናወን ያለበት መሆን፤
ለ. አዲስሠራተኞችየሚቀጠሩትግልጽ በሆነ ማመልከቻ በዉድድር፣ በፈተና እና በምዘና ሥርዐት ላይ ተመስርቶ ክፍት ቦታውን አስመልክቶ ከትምህርት፣፣ከብቃት፣ከሙያ፣ከልምድ፣ ከክህሎት፣ልዩ ችሎታ ከመልካም ሥራ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ቦታው የሚጠይቀውን ልዩ ችሎታን ብቃት አሟልተው መገኘታቸውሲረጋገጥመሆኑን፤
(ሐ) ከዳኞችውጭላሉሠራተኞችየሚፈከልክፍያብቃትያለቸውንሠራተኞችለመሳብናበሥራላይ ለማቆየት በቂ መሆኑን እና ክፍያውም መርሆዎችን መሠረት በማድረግ ልዩ ችሎታ ያላቸውን ሠራተኞችን ለመቅጠርና ለመሳብ በሚያስችል በብቃት ላይ በተመሰረተ ሥርዐት በየጊዜው የሚገመገምና የሚከለስመሆኑን፡፡
4) የአስተዳደር ሠራተኞች መብትና ጥቅማ ጥቅም በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ለሌሎች የመንግስት ሠራተኞች ከተፈቀደው ያነሰ ሊሆን አይችልም፡፡
39.ኦዲት
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሂሳብ መዝገብና የበጀት አጠቃቀም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 35 መሰረት መከናዎኑንበፌደራልዋናኦዲተርበየአመቱይመረመራል፡፡
ምእራፍስምንት
ስለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ
40.የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አንድ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ (ከዚህ በኋላ “ጉባዔ” እየተባለ የሚጠራ) ይኖራቸዋል፡፡
41.የጉባዔው አባላት
1) የጉባዔው አባላት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ኘሬዚዳንቶች፣ ምክትል ኘሬዚዳንቶች፣ የፌዴራል ጠቅላይፍርድቤትዳኞች፣በፌዴራልከፍተኛእናበመጀመሪያደረጃፍርድቤትዳኞችየተወከሉ ሁለት ዳኞች ከእያንዳንዳቸዉ አንድ ወንድ አንድ ሴት፤ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ኘሬዚዳንቶች፣የአዲስአበባእናየድሬድዋከተማፍርድቤቶችኘሬዚዳንቶችይሆናሉ፡፡
2) በጉባዔው ላይ ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ድምጽ የመስጠት መብት ሳይኖረዉ/ራት ይሳተፋል/ትሳተፋለች፡፡
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ያልተጠቀሱ ዳኞች እና አግባብ ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን፣ ማኀበራትን ፣ ድርጅቶችን ፣ ከፍተኛ የሕግ ትምህርት ተቋማት እና የሳይንስ ተቋሞችን የሚወክሉ ሰዎች ወይም ሌሎች ግለሰቦች በጉባዔው እንዲሳተፋ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊጋበዙ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ድምጽ የመስጠት መብት አይኖራቸውም፡፡
42.የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር
ጉባዔው ከዚህ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡
1)የዳኝነትነጻነት፣ገለልተኝነት፣ተጠያቂነትእናፍትህአስተዳደርረገድበኢትዮጵያበየትኛዉምቦታ ባጋጠሙችግሮችላይተወያይቶመፍትሔመስጠት፣
2) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዚህ አዋጅ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸዉ ህጎች የተሰጠዉ ደንብ እና መመሪያ የማዉጣት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አሠራርን ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን ማሳለፍ፣
3) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አዳዲስ ሕጎች እንዲወጡ ወይም ነባር ሕጎች እንዲሻሻሉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሣብ ማቅረብ፣
4) የዳኝነት ሥራ አካሄድን ለማቀላጠፍና ለማጠናከር የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን እና
5) ለጉባዔው ሥራ አፈፃፀም አስፈላጊውን ደንብ ማውጣት፡፡
43.የጉባዔው አሠራር ሥነ-ሥርዓት
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት የጉባዔው ሰብሳቢ ይሆናል/ትሆናለች፡፡
2) ጉባዔው የራሱን ፀሐፊ ይመድባል፡፡
3) ጉባኤዉ ስራዉን ለማከናዎን የሚረዱ ኮሚቴወችን ያዋቅራል
4) ጉባኤዉ የራሱ ላይዘን ቢሮ እና ተጠሪዎች አስፈላጊ በሆኑ ፍርድ ቤቶችያቋቊማል፣
5) ጉባዔው የሥራ ባልሆኑ ቀናት በዓመት አንድ ጊዜ ይሰበሰባል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ ስብሰባም መጥራት ይችላል:
6) ከጉባዔው አባላት ሁለት ሶስተኛው ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡ ውሣኔ በድምጽ ብልጫ ይተላለፋል፡፡ድምጽእኩልለእኩልበተከፈለጊዜየጉባዔውሰብሳቢወሳኝድምጽይኖራቸዋል።
ምእራፍ ዘጠኝ
የፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የጉዳዮች አስተዳደር
44.የፍርድ ቤት መር አስማሚነት
1) በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ የፍታብሄር ጉዳዮች ዉስጥ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያ የሚወሰኑ ጉዳዮችበፍርድ ቤቶቹ በሚቋቋም የፍርድ ቤት መር አስማሚነት በኩል እንዲያልፉ ይደረጋል።
2) ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት በኩል ጉዳያቸዉን በስምምነት ካልጨረሱ ይህንኑ የሚገልጽ በአስማሚዎቹ የተፈረመ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት በማቅረብ የፍርድ ሂደቱ እንዲቀጥል ይደረጋል።
3) የተስማሙ ከሆነ የስምምነቱ ሁኔታዎች በአስማሚዉ በግልጽ ተለይተዉ ከቀረቡ እና ተከራካሪዎቹከፈረሙበትቡሃላአስማሚዉይህንሰነድለፍርድቤትቀርቦእንዲጸድቅያደርጋል።
ሰነዱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ሰምምነቱ ለህግ እና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ቡሃላ እንዲጸድቅ ያደረጋል።
4) የጸደቀዉ የስምምነት ሰነድ እንደማንኛዉም የፍርድ ቤት ዉሳኔ ተፈጻሚ ይሆናል።
5) በአንደኛዉ ተከራካሪ ወገን ያለመቅረብ ምክንያት የመስማማት ሂደቱ ካልተሳካ አስማሚዉ ይህንኑ በመግለጽ ለፍርድ ቤቱ ሪፖርት ያደርጋል። መደበኛዉ የፍርድ ሂደትም ይቀጥላል።
6) በፍርድ ቤት መር አስማሚነትም ይሁን በሌላ አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴ ግራ ቀኙ ከተስማሙ በደንቡ መሰረት ወጭዎች ተቀንሰዉ የከፈሉት የዳኝነት ክፍያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7) የዚህን ድንጋጌ ለማስፈጸም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝርዝር መመሪያ ያወጣል።
45.ስለ አስማሚነት መርሆዎች
1) በፍርድ ቤት መር አስማሚነት የሚደረገዉ ማንኛዉም ሂደት በእኩልነት እና በባለጉዳዮቹን ሙሉ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።
2) በማስማማት ሂደቱ ተከራካሪ ወገኖች የሚሰጡት የእመነት ቃሎች ወይም ማንኛዉም ንግግሮች ለፍርድ ቤት በማስረጃነት አይቀርቡም። ለዚህም አስማሚዉ ማረጋገጫ ይሰጣል።
3) በፍርድ ቤት አስማሚነት በኩል የሚደረጉ ማናቸዉም የሃሳብ ልዉዉጦች ሚስጥራዊነት የተጠበቀ ነዉ።
46.ስለ አስማሚዎች
1) የአስማሚነት ስልጠና ወስደዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያወጣዉን ምዘና ያለፉ ቢያንስ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸዉ እና ከአምስት አመት ያላነሰ ጊዜ በህግ ሙያ ያገለገሉ አስማሚ ሆነዉ ሊመረጡ ይችላሉ።
2) የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተገለጸዉን ያሟሉ ባለሙያዎች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያዘጋጀዉ የአስማሚዎች ሮስተር መዝገብ ዉስጥ እንዲካተቱ ይደረጋሉ።
3) እንደአስፈላጊነቱ ፍርድ ቤቱ ቋሚ የሆኑ ወይም በጊዜያዊነት ብቁ አስማሚዎችን ሊቀጥር ይችላል።
47. ስለክፍያ
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 46 ንኡስ አንቀጽ (1) እና (2) የተገለጹ አስማሚዎች የጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያ የሚወሰን ለአስተዳደራዊ ጉዳይ እና አመታዊ ክፍያ ይከፍላሉ።
2) አስማሚዎች በባለጉዳዮች ተመርጠዉ የማስማማት አገልግሎት ከሰጡ ተገቢዉ ክፍያ ይከፈላቸዋል።
3) በማስማመቱ ሂደት ዉስጥ የሚያልፉ ባለጉዳዮች ለፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተገቢዉን ክፍያ ይፈጽማሉ።
4) ክፍያን በሚመለከት ዝርዝር መመሪያ በጠቅላይ ፍርድ ይወጣል።
48.የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር
1) የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡላቸዉን ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ወይም የሚጠናቀቁበትን የጊዜ ሰሌዳ ገደብ በማስቀመጥ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓቱ የተሳለጠ እና ጥራቱ የሚረጋገጥበት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ተግባራዊያደርጋሉ።
2) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተገለጸዉን ለማስፈጸም ዝርዝር መመሪያ ያወጣል።
49.በቴክኖሎጅ የተደገፈ የመዝገብ አመራር ስርአት ስለመዘርጋት
1) የፌደራል ፍርድ ቤቶች በማንኛዉም የፍርድ ቤት ደረጃ የሚቀርቡ የፍታብሄር ወይም የወንጀል ጉዳይ ክርክሮች አዳዲስ የመረጃ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ዳጂታል ወይም አዉቶሜትድ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ስርዓት ሊዘረጉ ይችላሉ።
2) ተከራካሪ ወገኖች በተዘረጋዉ ስርኣት መሰረት ክርክሮቻቸዉን የማካሄድ ግዴታ አለባቸዉ።
3) ዝርዝሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያ ይወሰናል።
ምእራፍ አስር
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
50.የፍርድ ቤት ውሣኔዎችና ትዕዛዞች
1) በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በህግ እስካልተለወጠ ድረስ የፀና ሆኖ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2) የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸዉን ዉሳኔዎች ወይ ተእዛዞች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ዉስጥ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ በማንኛዉም ክልል ዉስጥ የሚገኝ የመንግስት አካል፣ተቋም ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም ማንኛዉም ሰው ውሳኔዎቹን ወይም ትእዛዞቹን የመፈጸም እና የማስፈጸም ግዴታ አለበት።
3) ማንኛዉም ሰዉ በዚህ አዋጅ የተጣለበትን ግዴታ የማይወጣ ከሆነ በዚህ አዋጅና አግባብ ባለው ሌላ ህግ ተጠያቂ ይሆናል።
4) አንድን ጉዳይ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የክልል ወይም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ወይም የአዲስ አበባ ወይም የድሬዳዋ ከተሞች ሥልጣናችን ነው ብለው የያዙት ወይም ሥልጣናችን አይደለም ብለው የመለሱት እንደሆነ ስልጣኑን በሚመለከት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገቢውን ትዕዛዝ ይሰጥበታል፡፡
51.ቅጣት
1) የፍርድ ቤት ወይም የዳኞችን በነጻነት መስራት የሚጋፋ ወይም በዳኞች ላይ ተጽእኖ የሚያደርግ ወይም ለማድረግ የሞከረ ማንኛው ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከሦስት ወር እሥራት ባላነሰ ከሁለት አመት ባላበለጠ ጽኑ እስራት ይቀጣል።።
2) የፍርድ ቤትን ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ የማይፈጽም ወይም ለመፈጸም መሰናክል የሚፈጥር ወይም ሲጠየቅ ለመፈጻም ተባባሪ የማይሆን ማንኛዉም ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከሁለት አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል።
52.የዉጭ አማካሪ ምክር ስለማደራጀት
1) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀድሞ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ከፍተኛ ልምድ እና ብቃት ካላቸዉ የህግ ባለሙያወች፣ ከዩኒቨርስቲ ምሁራን የተዉጣጡ ያለክፍያ የሚሰሩ የዉጭ አማካሪዎችን በመምረጥ የዳኝነት ስርዓት የዉጭ አማካሪ ምክር ቤት ሊያደራጅ ይችላል።
2) የአማካሪ ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ስርዓት ለማሻሻል የሚረዱ አስገዳጅ ያልሆነ ምክር ሃሳቦችን በማመንጨት እንዲሁም ሌሎች በፍርድ ቤቱ የሚሰጡትን ስራዎች በማከናወንየፍርድ ቤቱን አስተዳደርያግዛል።
3) አማካሪ ምክር ቤቱ ስራዉን በሚያከናዉንበት ጊዜ የዳኝነት ነጻነትን እና የዳኝነት ስነምግባርን በማይጻረር መልኩ በጥብቅ ዲስፕሊን እና በከፍተኛ ሀላፊነት ስራቸዉን ማከናዎን ይጠበቅባቸዋል።
4) ዝርዝሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያ ይወሰናል።
53.ስለ ይግባኝ ማስፈቀጃ
1. ማንኛዉም በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ቅር የተሰኘ ሰዉ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊጠይቅ የሚችለዉ ዉሳኔዉን ከሰጠዉ ፍርድ ቤት የይግባኝ ፈቃድ ሲያገኝነዉ።
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ተግባራዊ የሚሆነዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣዉ መመሪያ ተለይተዉ በሚወሰኑ የፍታብሄር ጉዳዮች ላይ ብቻ ነዉ።
54.ደንብ እና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን፡፡
1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጥሎ የተጠቀሱትን በተመለከተ ደንብ እና መመሪያ ማውጣት ይችላል፡፡
ሀ) ለሰበር የማይቀርቡ አነስተኛ መጠን ያላቸዉን ጉዳዮች ለ) ስለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ገንዘብ አከፋፋል ፤
ሐ)በፍርድቤትበሚደረግክርክርስለሚከፈልቅጣት፣ስለወጪናኪሣራአከፋፈልእና መ)የፌደራልጠቅላይፍርድቤትሰበርሰሚችሎትየችሎትአመራርስነስርዓትደንብ
2) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ አዋጅ ላይ የተጠቀሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ደንብ እና መመሪያ ማውጣት ይችላል፡፡
55.የመሽጋገሪያ ድንጋጌዎች
1) ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት የተጀመሩ ጉዳዮች በተጀመሩበት ፍርድ ቤት እና በነባሩ ህግ መስተናገዳቸዉ ይቀጥላል።
2) በዚህ አዋጅ ከአንቀጽ 11 እስከ አንቀጽ 15 ድረስ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት አዋጁ ከጸደቀ ከ6 ወር ቡሃላ ይሆናል።
3) የአስተዳደር ሠራቶኞች መተዳደሪያ ደንብ እስከሚወጣ ድረስ የሠራተኞች ቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ እድገትና አስተዳደር የዚህን አዋጅ መርሆዎች ሳይቃረን ቀድሞ ሲሰራበት በነበረው ሕግ መሰረት ይቀጥላል፡፡
56.የተሻሩ እና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች
1)በዚህአዋጅአንቀጽ4ዐላይየተጠቀሰውእንደተጠበቀሆኖ፣

የፌዴራል ፍርድቤቶችአዋጅቁጥር
25/1988 እናአዋጁንለማሻሻልየወጡቁጥራቸው138/1991፣254/1993፣321/1995 እና
454/1997 የሆኑ አዋጆች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡፡
2) ይህን አዋጅ የሚቃረን ወይም በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን የሚመለከት ማናቸውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
የፌዴራል ፍርድቤቶችአዋጅቁጥር
25/1988 እናአዋጁንለማሻሻል የወጡ ቁጥራቸው 138/1991፣254/1993፣321/1995 እና
454/1997 የሆኑ አዋጆች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡፡
2) ይህን አዋጅ የሚቃረን ወይም በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን የሚመለከት ማናቸውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

No comments:
Post a Comment